We seek your help to build the House of God in Wellington, New Zealand. ኑ የእግዚአብሄርን ቤት በአንድነት እንሥራ!
Wellington
በስመ አብ ወወልድ ውመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክአሜን።
በመላው ዓለም ለምትገኙ የኦቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ መንፈሳዊ የበረከት ጥሪ !!!
"ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው " የሐ ሥራ 20:35
በምስራቅ አውስትራልያና ኒውዚላንድ ሀገረ ስብከት የምትገኘው በኒውዚላድ የዌሊንግተን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያምን ቤተ-ክርስቲያንን ለመሥራት በምናደርገው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የበኲልዎን አስተዋጽኦ በማድረግ የታሪክ በለቤት ይሁኑ።
የዌሊንግተን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን በስደት በመጡ ምእመናን ለረዥም ጊዜ በመሰባሰብ እግዚአብሔርን በማምለክ የቆዩ ሲሆን ከመስከረም 2011ዓ ም ጀምሮ እ አ አ በ2018 በእመቤታችን ምልጃ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድና በወቅቱ የአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ መልካም ፈቃድ ከብዙ ጥረትና ድካም በኋላ ታቦትና ቋሚ ካህን ከኢትዮጵያ በማምጣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሙሉ ሁና ተመሥርታ ቋሚ መንፈሳዊ አግልግሎት መስጠት ከጀምረች አራት ዓመታትን አስቆችራለች ።
ላለፉት አራት አመታት እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ በኪራይ ቤት ታቦቱንና ነዋየ ቅድሳቱን ከሰው ጋር በማዳበል አግልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በልዑል በእግዚአብሔር ፈቃድ ከመስከረም 17/1/2015 ዓ ም ጀምሮ ለቤተ-ክርስቲያናችን 5.2 ሄክትራ መሬትና መኖሪያ ቤት የገዛን ሲሆን ነገር ግን ቤተ-ክርስቲያን ለመስራትና ለአገግሎት ለመዘጋጀት በአጥቢያ ምእመናን አቅም የሞርጌጅ ክፍያ ከፍሎ ቤተ-ክርስቲያን ለመሥራት እጅግ ከአቅም በላይ በመሆኑ ይህንን ጎፈንድሚ መክፈት አስፈልጓል ።
እንደሚታወቀው በየትኛውም ዓለም ያለችው ቤተ-ክርስቲያን የአንዱ የክርስቶስ አካል እንደመሆኗ በየትኛውም ዓለም የምትገኙ ምእመናን አቅማቹ በፈቀደው መጠን በምትችሉት ሁሉ እንድትረዱ በልዑል እግዚአብሔር ስም እየጠየቅን ለሌሎችም መልእክቱን እንድታስተላልፉ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም እንማጸናለን።
ማወቅ የምትፈልጉ ማንኛውም ጥያቄ ከታች ባለው አድራሻ የሰበካ ጉባኤውን መጠየቅ ይችላል። ቤተክርስቲያኗ ደግሞ በህጋዊ መልኩ በሃገር ኒዉዚላንድ በበጎ አድራጊዎች መዝገብ የተመዘጋበች ሲሆን፣ የሰበካ ጉባኤዉም ስማቸው በህጋዊ ተመዝግበው ይገኛሉ:
https://www.register.charities.govt.nz/Charity/CC53577
Abba Teklesilassie Bokan: The Head Priest - +642041429913
Dicon Dawit Shafe: Spiritual Services Coordinator - +642108282278
Mr Robel Assefa Mengiste: Deputy chair - +64223097399
Mrs Elshaday Mamo: Treasurer - +642041007865
Mr Eyob Teshome: Secretary - +642041423080
Mr Gzachew Mengistu Ayele: Public Relations - +642040393137
Mrs Martha Belayneh: Accountant 1 - +642102583050
Mrs Mahlet Woldesilasse: Accountant 2 - +642041004570
Greetings to all Christians in New Zealand and abroad. We are asking for any dollar contribution to build the House of God together. We have been saving funds from members' contributions for many years and with the help of God, we recently bought a 5.2 hectar land with a residential house. Now, we are reaching out to all Christian families in New Zealand and overseas to help us reach the target build a church and assembly hall.
Thank you for your help in advance. You have no idea how much it means to us to have your support.
May God bless you all !
For more information, please contact one of the officers listed above.
The Ethiopian Orthodox Tewahido Church in Wellington was established by a small group of former refugees and migrants from Ethiopia who have chosen Wellington as home.
እግዛብሄር ይስጥልን፣ እመቤቴ ትጎብኛችሁ 28 March 2022
የተወደዳችሁ የእግዛብሄር ቤተሰቦች፣ የተሰበሰበው እርዳታ $10279 NZD ደርሷል! ክብር ምስጋና ለእግዚአብሄር ይሆን፣ ይህ ሁሉ የእናንተ ውጤት ነው፣ በያላችሁበት እመቤቴታችን ትጎብኛችሁ።
የቤተክርስቲያናችን አምባሳደሮች ናችሁ!
አሁን ደግሞ በዚህ ወር ለምታውቁት አንድ ምዕመን፣ቤተሰብ/ጓደኛ የበረከቱ ተካፋይ እዲሆኑ እንድትጠይቁልን በትህትና እንጠይቃለን።
እግዚአብሄር ከረዳን ባለን ገንዘብ የቤተክርስቲያን መሥሪያ የሚሆን ቦታ / ቤት ለመግዛት እንቅስቃሴ ጀምረናል። በጸሎት አግዙን።
የደረስንበትን በየጊዜው እናሳውቃችኋላን።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር
ሰበካ ጉባኤው
Your message will be displayed on the page and emailed to the donor.
Your new message will also be emailed to the donor.
Saving a blank entry will delete the current comment.