እግዛብሄር ይስጥልን፣ እመቤቴ ትጎብኛችሁ
28 March 2022የተወደዳችሁ የእግዛብሄር ቤተሰቦች፣ የተሰበሰበው እርዳታ $10279 NZD ደርሷል! ክብር ምስጋና ለእግዚአብሄር ይሆን፣ ይህ ሁሉ የእናንተ ውጤት ነው፣ በያላችሁበት እመቤቴታችን ትጎብኛችሁ።
የቤተክርስቲያናችን አምባሳደሮች ናችሁ!
አሁን ደግሞ በዚህ ወር ለምታውቁት አንድ ምዕመን፣ቤተሰብ/ጓደኛ የበረከቱ ተካፋይ እዲሆኑ እንድትጠይቁልን በትህትና እንጠይቃለን።
እግዚአብሄር ከረዳን ባለን ገንዘብ የቤተክርስቲያን መሥሪያ የሚሆን ቦታ / ቤት ለመግዛት እንቅስቃሴ ጀምረናል። በጸሎት አግዙን።
የደረስንበትን በየጊዜው እናሳውቃችኋላን።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር
ሰበካ ጉባኤው